ለኤንጅን ሰማያዊ ጭስ ምክንያት ምንድነው?
Category : Nano
💥 ለኤንጅን ሰማያዊ ጭስ ምክንያት ምንድነው?
🔴 ለሰማያዊ ጭስ ዋና ምክንያት ዘይት ወደ ሲሊንደር መግባትና ከነዳጅ ጋር ተደባልቆ መንደዱ ነው፡፡
ይህም ኤንጅኑ እያረጀ ሲሄድ ወይም ሲል እና ጋሰኬት ሲበላ ይከሰታል፡፡ ልብ በል! የተጋነነ ሰማያዊ ጭስ
ለማየት እጅግ ጥቂት ዘይት መቃጠል በቂ ነው፡፡
🔵 ኤንጅን ሲነሳ ብቻ የሚታይ ሰማያዊ ጭስ ካጋጠመህ የቫልቭ ጓይና ሲል ወይም የቫልቭ ጓይና መበላትን
ያመላክታል፤ ይህም ሲነሳ ለሚከሰት መንጓጓት ምክንያት ሊሆንም ይችላል፡፡
🔵 ለሰማያዊ ጭስ መከሰት ሌሎች ምክንያቶችም አሉ እኒህም፡-
✔ የፒስተን፣ ፋሻ እና ካምቻ መበላት፣
✔ ፒሲቪ ቫልቭ መቆሸሸ ወይም መበላሸት፣
✔ የተቀጣጣይ ነዳጅ/አየር መተላለፊያ ቱቦ ካስኬት ማፍሰስ፣
✔ የኤንጅን የዘይት ሲል መበላት እና የቴስታታ ጓርንሲዮን መቃጠል ናቸው፡፡
🔴 የቆሸሸ የዘይትና የአየር ፊልትሮ መጠቀም ለዘይት ፍሰት፣ መባከን እና ለሰማያዊ ጭስ መከሰትም ምክንያት
ናቸው፡፡ ዘይት በሞቀው የኤንጅን የውጭ አካል (ጭስ መተላለፊያ ቱቦ) ላይ በሚፈስበት ጊዜም ሰማያዊ
ጭስ ይከሰታል፡፡
🔵 የዘይት ወደ ሲሊንደር መለቀቅ የኤንጅንን መንተፋተፍ፣ መንጓጓት እና የካንዴላ መርጠብን ይፈጥራል፡፡
🔵 በሰማያዊ ጭስ መልክ የሚታየው በኤንጅን ውስጥ የሚከሰት የዘይት ፍሰት የኤንጅን ጉልበት መቀነስ እና
የዘይት መጉደልን ያስከትላል ፡፡
🔵 በኤንጅን ውስጥ የሚከሰት የዘይት ፍሰት ነዳጅ ከዘይት ጋር እንዲደባለቅ ብሎም የዘይትን ባህሪ
በመለወጥ የማለስለስ ተግባሩን በአግባቡ ማከናወን እንዲሳነው ያደርጋል፤ ዝቃጭም ይፈጥራል፡፡
💥 የሰማያዊ ጭስን ለማስወገድ ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት
💚 ደረጃ 1– ወቅቱን ጠብቆ ያልተለወጠ የቆሸሸ ዘይት ወይም የኤንጅን የብልሽት መከላከል ጥገና በወቅቱ አለመከናወን ሳቢያ የሚፈጠረው የዘይት ዝቃጭ የዘይት ማስወገጃ ቱቦን በመድፈን ዘይት በቴስታታው ወለል ላይ እንዲከማች ያደርጋል ብሎም በቫልቭ ጋይድ ሲል አልፎ ወደ ሲሊንደር ይገባል፣ ይቃጠላል፣ ሰማያዊ ጭስ ይከሰታል፡፡
👉 ይህን ለማስወገድ ወቅቱን ጠብቀህ ዘይት፣ የዘይት እና የአየር ፊልትሮ ለውጥ፤ ዝቃጭን አስወግድ
💚 ደረጃ 2- ማንኛውም ኤንጅን ፒሲቪ/ፖሲቲቭ ክራንክ ኬዝ ቬንቲሌሽን/ ማለትም በዘይት ገንዳ ውስጥ የሚከሰትን እምቅ ማሰተንፈሻ ሲስተም አለው፤ ለዚህ ተግባር የሚያገለግሉ ቱቦዎች ሲላሉ፣ ሲዘጉ፣ ወይም ቫልቩ ሲበላሽ ከታመቀው ተቀጣጣይ ጋዝ ጋር ዘይት ተደባልቆ ወደ ሲሊንደር እንዲለቀቅ በማድረግ፣ ይቃጠላል፣ ሰማያዊ ጭስ ይከሰታል፡፡
👉 ይህን ለማስቀረት የፒሲቪ ሲሰተምን ፈትሽ፣ ቱቦ እና ቫልቩን አጽዳ ወይም ለውጥ
💚 ደረጃ 3- ኤንጅን እያረጀ ሲሄድ ፋሻ እና ካምቻ ይበላል በዚህም ዘይትን መቆጣጠር ሰለሚሳነው በሲሊንደር ቀርቶ ከነዳጅ ጋር እንዲቃጠል ሰለሚያደርግ ሰማያዊ ጭስ ይከሰታል፡፡
👉 ይህን ለማወቅ ቀላሉ መንገድ ካንዴላውን ፈተህ ጫፉን ማየት ነው፡፡ ዘይት ጫፉ ላይ ካየህ ወይም ከረጠበ ኤንጅኑ እድሳት ይፈልጋል ማለት ነው፡፡
👉 ለዚህ ናኖ ኢነርጃይዘር በመጠቀም ይህን ችግር አስወገድ
💚 ደረጃ 4- የቫልቭ ጓይና ሲል ከተበላ ዘይት ወደ ሲሊንደር እንዲለቀቅ በማድረግ፣ ይቃጠላል፣ ሰማያዊ ጭስ ይከሰታል፡፡
👉 ይህ ካጋጠመህ የቫልቭ ጓይና ሲል በመለወጥ ይህን ችግር አስወገድ።
👉 ልብ በል ሲል ለመለወጥ ቴስታታ ማውረድ አያስፈልግም።
ለተጨማሪ መረጃ ናኖ ቴክ ኢስት አፍሪካ 0911408625፡ 0911833396 ይደውሉ ወይም facebook page Nano Tech East Africa ይጎብኙ