በየጊዜው የሚነሱ ጥያቄዎች

ናኖ ኢነርጃይዘርን አስመልክቶ በየጊዜው ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ

ናኖ ኢነርጃይዘር የመኪና መድኃኒት ነው፡፡ መኪና ሲጮህ፣ ሲርገፈገፍ፣ ሲያጨስ፣ ነዳጅና ዘይት ሲበላ፣ ጉልበቱ ሲደክም፣ “ሲታመም” ናኖ ኢነርጃይዘር “ያድነዋል”

ናኖ ኢነርጃይዘር ልክ እንደ ህመም መከላከያም ሲለሚያገለግል መኪና ከቶም “አይታመምም”፡፡ የመኪናው አካላት ወለል ላይ መከላከያ ሰለሚፈጥር ወደፊት ሊያጋጥም የሚችለውን ብልሽት ያስቀራል፡፡ አንዴ ናኖ ኢነርጃይዘር ከተጠቀመ የሚበላው አካል ወለል በሴራሚክ ሜታል ሰለሚሸፈን በዘይት ውስጥ ናኖ ኢነርጃይዘር ባይኖርም የታከመው አካል ለረጂም ጊዜ ሳይበላ ይቆያል፡፡

1.  በናኖ ኢነርጃይዘር የሚፈጠረው የሴራሚክ ሜታል ወለል ውፍረት ምን ያህል ነው?

ናኖ ኢነርጃይዘር የተበሉ አካላት ወለል ላይ የሚያስቀምጠው የሴራሚክ ሜታል ወለል በአቶም ደረጃ ሳይሆን በፓምፕ አካላት ላይ በማይክሮን ( ˃ 0.001 ሚ.ሜ) ፣ ካምቻና እና ፋሻ ላይ በርካታ የሚሊ ሜትር መቶኛ ( ˃ 0.01 ሚ.ሜ.) እና በጥርሳጥርስ ላይ በርካታ የሚሊ ሜትር አስረኛ ( ˃ 0.1 ሚ.ሜ.) ውፍረት ይኖርዋል፡፡

2.  በናኖ ኢነርጃይዘር የሚፈጠረው የሴራሚክ ሜታል ወለል ውፍረት የመጨመር ስጋት የለም? በዝቶ ኤንጅኑ አይነክስም?

በጭራሽ! ምክንያቱም የሴራሚክ ሜታል ወለል የሚፈጠረው ተቀናጅተው  በሚሽከረከሩ አካላት መካከል በተፈጠረው ሰበቃ ሳቢያ ሲሆን ወለሉ ከተፈጠረ በኃላ ሰበቃው በከፍተኛ መጠን ስለሚቀንስ የወለሉ እድገት ይቆማል፡፡ ስለሆነም የወለሉ ውፍረት በዝቶ ኤንጅኑ አይነክስም፡፡

3.  ናኖ ኢነርጃይዘር በመጠቀም ጠንካራ የሴራሚክ ሜታል ወለል ይፈጠራል፡፡ ይህን ወለል ነገ መፋቅ ብንፈልግ ይቻላል?

የቻላል! የሴራሚክ ሜታል ወለል ውፍረት እጅግ አነስተኛ ሲሆን የሚፍቀው ቱል የሚሊ ሜትር አስረኛ ጀምሮ መፋቅ ሰለሚችል የሴራሚክ ሜታል ወለሉን ማንሳት ይችላል፡፡

4.  የሴራሚክ ሜታል ወለል በአገልግሎት ምክንያት ይቀረፍ ይሆን?

የሴራሚክ ሜታል ወለል በአገልግሎት ምክንያት በፍጹም አይቀረፍም፡፡ ብረት ከሴራሚክ ሜታል ጋር ከ 10 እስከ 30 ማይክሮን ጥልቀት ተዋህዷል፡፡ የብረቱ ወለል መጨረሻ ወይም የስራሚክ ሜታል ወለል መነሻ የተለየ መጋጠሚያ ወለል የሚባል ስለሌለ፤ የሴራሚክ ሜታል ወለል ለመቀረፍ መሠረታዊ ምክንያት የለም፡፡

5.  በገበያ የሚሸጡ በዘይት ውስጥ የሚጨመሩ ፈሳሾች የዘይት ፊልትሮን ይዘጋሉ ይባላል፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘርስ አይዘጋም?

የለም! ናኖ ኢነርጃይዘር በቀላሉ ከዘይቱ ጋር ቢደባለቅም የዘይቱን ውፍረትም ሆነ ባህርይ አይለውጥም፤ መጠኑ 20 ናኖ ሜ. (የሚ.ሜ. አንድ ሚሊዮንኛ) በመሆኑ በቀላሉ በፊልትሮ ውስጥ አልፎ ወደ ተበሉ አካላት በቀጥታ ይሄዳል፡፡

6.  መኪናዬ በአምራቹ የተሰጣት የዋስትና ጊዜ ገደብ ውስጥ እያለሁ ናኖ ኢነርጃይዘር መጠቀም እችላለሁ?

የሚከለክልህ ምንም ምክንያት የለም፤ መኪናው ከፋብሪካ እንደወጣ ናኖ ኢነርጃይዘር ቢጠቀም ይመረጣል፡፡ የኤንጅን አካላት አዲስ ሲሆኑ ናኖ ኢነርጃይዘር የበለጠ ውጤታማ ይሆናል፡፡ ለስላሳ፣ ጠንካራ፣ ከሰበቃ ነጻ የሆነ እና የማይፋቅ ወለል በላያቸው ላይ ይፈጥራል፡፡

7.  ናኖ ኢነርጃይዘር ተጠቅመው እስከ 50000 ኪ.ሜ. ያለ እንከን ይጠቀማሉ ሲል ምን ማለት ነው?

መኪናውን በአግባቡ ከተጠቀሙበት ናኖ ኢነርጃይዘር የፈጠረው የሴራሚክ ሜታል ወለል እስከ 50000 ኪ.ሜ. አይፋቅም ማለት ነው፡፡

8.  ናኖ ኢነርጃይዘርን መቼ ብጠቀም የተሻለ ይሆናል?

መኪናው እየሰራ እያለ በማናቸውም ጊዜ ናኖ ኢነርጃይዘር መጠቀም ይቻላል፡፡ ዋናው ቁምነገር መኪናው የሚነዳ /ኤንጅኑ ያልነከሰ/ መሆኑ ነው፡፡ ለነገሩ መኪናው ከፋብሪካ ከወጣበት እለት ጀምሮ ናኖ ኢነርጃይዘር መጠቀም ጥሩ ነው፡፡

9.  የተፋቀ ወይም የለሰለሰ ካምቻ ላይ ናኖ ኢነርጃይዘር ብንጠቀም ምን ይሆናል?

የተፋቀ ወይም የለሰለሰው ካምቻ ላይ ናኖ ኢነርጃይዘር ብንጠቀም ከፍተኛ የስራ ጫና ያለበትን አካል (የካምቻው የላይኛው ጠርዝ) ለይቶ የበለጠ ጠንካራና ለስላሳ ያደርገዋል፡፡

10.  ናኖ ኢነርጃይዘር ተጠቅሜ መኪናው ዘይት ሳይኖረው መንዳት እችላለሁ?

በፍጹም አትሞክር! የመኪና ዘይት ማለስለሻ ቅባት ብቻ ሳይሆን አካላትን ለማጽዳት፣ ለማቀዝቀዝ እና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ለማከናወን ጭምር ነው፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር የሚጨመረውም ዘይት ውስጥ ሲሆን ስራውን ሲጨርስ ዘይት መኖሩ የግድ ነው፡፡

ናኖ ኢነርጃይዘር ዲዛይን ሲደረግ ያለ ዘይት መኪና መንዳትን ታሳቢ አድርጎ ሳይሆን የአካላትን የአገልግሎት ዘመን ለማራዘም እና አስተማማኝ ለማድረግ ነው፡፡

ናኖ ኢነርጃይዘር ተጨምሮበት የተፈቀደውን ኪ.ሜ. (እስከ 10 ሊ. ዘይት ለሚጠቀም 1200 ኪ.ሜ. ከ 10 ሊ. በላይ ለሚጠቀም 3000 ኪ.ሜ.) በላይ የተነዳ መኪና ምናልባት የዘይት መፍሰስ ቢያጋጥመው በወቅቱ ዘይት መጨመር ባይቻል ወደ ሚቀጥለው ዘይት መሸጫ እሰኪደርስ ድረስ (እስከ 100 ኪ.ሜ.) ያለምንም ችግር ሊነዳ ይችላል፡፡

ጋዜጠኞች እና ታዋቂ ባለሙያዎች ባሉበት በሙከራ ማዕከል ናኖ ሴራሚክ ሜታል ውህድ የተጠቀመን አንድ መኪና ያለ ዘይት ከ 560 ኪ.ሜ. በላይ በመንዳት የሴራሚክ ሜታልን የተለየ ባህርይ ማሳየት ተችሏል፡፡

11.  ናኖ ኢነርጃይዘር ውጤት እስከ መቼ ድረስ ይቆያል?

በሙከራ እንደታየው ናኖ ኢነርጃይዘር ተጨምሮ (ከ 1200 ኪ.ሜ. እስከ 1500 ኪ.ሜ. ለአነስተኛ መኪና እና 3000 ኪ.ሜ. ለከባድ መኪና) ሲነዳ በተንቀሳቃሽ አካላት ላይ የሴራሚክ ሜታል ወለል ይፈጠራል፡፡ ይህ ወለል ሳይፋቅ እስከ 50000 ኪ.ሜ. ድረስ አገልግሎት ላይ ይቆያል፡፡ ስለዚህ በየ 50000 ኪ.ሜ. ናኖ ኢነርጃይዘር እየጨመሩ መኪናዎን ላልተወሰነ ጊዜ ያለእንከን መጠቀም ያስችሎታል፡፡

12.  ናኖ ኢነርጃይዘር ለመጠቀም የትኛው ዘይት የተሻለ ነው፣ አሮጌ ወይስ አዲስ፣ ሲንተቲክ ወይስ ሚኒራል?

የትኛውንም ዘይት መጠቀም ትችላለህ፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር ዘይትን የሚፈልገው ወደ ተለያዩ የሚኪና አካላት ተሸክሞ እንዲወስደው ብቻ ነው፡፡ ከዘይት ጋር አይዋሃድም፣ የዘይትን ባሕሪ አይቀይርም፤ አሮጌ ዘይት ውስጥ ከተጨመረ ናኖ ኢነርጃይዘር የሴራሚክ ሜታል ወለል ለመፍጠር የሚወደስድበት ጊዜ እስኪጨርስ ድረስ ዘይቱ ሳይፈስ መቆየት አለበት፡፡

13.  ያገለገለ መኪና ነው የገዛሁት ከዚህ ቀደም ምን አይነት ዘይት እንደተጠቀሙ አላውቅም አሁን ናኖ ኢነርጃይዘር መጠቀም እችላለሁ?

ትችላለህ! ቀደም ሲል የተጠቀሙት ዘይት አይነትም ሆነ ተጨማሪ ኦይል ትሪትሜንት መጠቀማቸው በናኖ ኢነርጃይዘር ላይ የሚያመጣው እክል የለም

14.  ናኖ ኢነርጃይዘር ተጠቅሜ መኪናውን ሳልነዳው ብቆይ ዘይት ውስጥ ዘቅጦ ይበላሽ ይሆን?

አይበላሽም! ናኖ ኢነርጃይዘር አይዘቅጥም፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር ጨምረህ ኤንጅኑ ከ 2 እሰከ 5 ደቂቃ ይስራ፣ ይህን ጊዜ ከዘይቱ ጋር ሙሉ በሙሉ መደባለቅ ይችላል፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር የሴራሚክ ሜታል ወለል የሚሰራው ኤንጅኑ እየሰራ ስለሆነ እስከ ተወሰነው ኪ.ሜ. ወይም ሰኣት ድረስ ቢሰራ ውጤቱን ቶሎ ታገኛለህ፡፡

15.  የመኪናዬ ኤንጅን እየሰራ የዘይት ግፊት ማሳያ መብራት ብልጭ ድርግም ትላለች፣ይህን ናኖ ኢነርጃይዘር ማስተካከል ይችላል?

የዘይት ግፊት ለመቀነስ ብዙ ምክንየቶች አሉ፤ ከሴንሰር መበላሸት እስከ የዘይት ፓምፕ፣ ቦኮላ ወይም ሻፍት መበላት ድረስ፤ ብልሽቱ የከፋ ካልሆነ ናኖ ኢነርጃይዘር ያክመዋል፡፡

ናኖ ኢነርጃይዘር የዘይት መበላትን/መባከንን ሙሉ በሙሉ ያስቆማል?

ለዘይት መበላት/መባከን ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ የፋሻ እና ካምቻ መበላት፣ የፋሻ መቀርቀር/መሰበር፣ የቫልቭ ሲል መበላት፣ ኦይል ሲል መበላት፣ የፒሲቪ ሲስተም መበላሸት፣ ወዘተ፡፡

ናኖ ኢነርጃይዘር የፋሻና ካምቻ መበላትን ይሞላል፤ የተቀረቀረ ፋሻን ያሰተካክላል፣

የተሰበረ ፋሻ ካለ በአዲስ መለወጥ አለበት፤ ቫለቭ ሲል እና ኦይል ሲል ከተበላ በአዲስ መለወጥአለበት፤ የፒሲቪ ሲሰተም ችግር ካለም ችግሩ መሰተካከል አለበት፡፡

17.  ናኖ ኢነርጃይዘር የነዳጅ መበላትን እንዴት ይቀንሳል?

ለአሮጌ መኪኖች ነዳጅ መብላት ዋና ምክንያት የኤንጅኑ ፋሻ እና ካምቻ መበላት እና ኮምፐሬሽን መቀነስ ሲሆን ናኖ ኢነርጃይዘር ይህን ስለሚያስተካክል ነዳጅን መቆጠብ ይቻላል፡፡ አዲስ ኤንጂን ላይ ናኖ ኢነርጃይዘር የተንቀሳቃሽ አካላት መካከል ያለውን ክፍተት በማሻሻል እና ሰበቃን በመቀነስ ነዳጅ ይቆጥባል፡፡

18.  ናኖ ኢነርጃይዘር ከኤንጅኑ የሚለቀቀውን ጭስና በካይ ጋዝ መቀነስ ይችላል?

ጭስና በካይ ጋዝ ከመጠን በላይ የመሆን ምንጭ የነዳጁ ጥራት፣ የነዳጅ ፓምፕ እና ከሱ ጋር የሚገናኙ አካላት ቅንብር ሲሆን ዋናው ምክንያቱ ግን የአካላት መበላት ነው፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር የኤንጅኑን የተበሉ አካላት ሰለሚያድሰ ከኤንጅኑ የሚለቀቀውን ጭስና በካይ ጋዝ በዘጠኝ እጥፍይቀንሳል፡፡

19.  ናኖ ኢነርጃይዘር ውጤት እንዴት ማወቅ ይችላል?

መኪናው በሚነዳበት ጊዜ የኤንጅኑ ጉልበት፣ ፍጥነት መጨመር፤ በቀላሉ ማርሽ እየለዋወጡ ማሽከርከር እና የጩሀት መቀነስ፤ ወዘተ ናቸው፡፡ ይህን ውጤት ናኖ ኢነርጃይዘር ጨምሮ ከ 500 እሰከ 1000 ኪ.ሜ. ከተነዳ በኃላ ይታወቃል፡፡

20.  ናኖ ኢነርጃይዘር ሁሉንም ኤንጅን ያድሳል?

በሚገባ! ሁሉም አይነት ኤንጅኖች ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ ጋዝ፣ ባዮፊዩል፣ ወዘተ የሚያቃጥሉ፤ ካርቡሬተር፣ ኢንጀክሽን፣ ቱርቦ፣ ወይም ሌላ የተገጠመላቸው፤ የሚሽከረከሩ (ያልነከሰ) እስከሆነ ድረስ በናኖ ኢነርጃይዘር ይታደሳሉ፡፡

21. ናኖ ኢነርጃይዘር መቼ ይጨመራል? ኤንጅኑን ሙሉ በሙሉ ማደስ ይችላል?

ናኖ ኢነርጃይዘር በማናቸውም ጊዜ መጨመር ይቻላል፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር የኤንጅኑን ማናቸውም ብረት ነክ አካላት የተበላ ወለል ያድሳል፡፡

22. ናኖ ኢነርጃይዘር ቱርቦን ያበላሽ ይሆን?

በፍጹም! እንዳውም ናኖ ኢነርጃይዘር ቱርቦን ከመበላሸት በመከላከል ረጂም እድሜ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ቱርቦ ዲዛይን ሲደረግ ጁርናል ቤሪንጉ በዘይት እንዲለሰልስ ታስቦ ነው፡፡ ቱርቦው ሲነሳና ሲቆም የዘይት ማለስለስ ተግባር ሰለሚታወክ ቤሪንጉ በይበልጥ መበላት ያጋጥመዋል፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር ቤሪንጉ ላይ መከላከያ ወለል ሰለሚፈጥር በዘይት የማለስለስ ተግባር መታወክ ሳቢያ የሚከሰተውን መበላት ያስቀረዋል፡፡

23. ካምቢዮ፣ ትራንስሚሽን፣ ዲፈረንሻል አላስፈላጊ ድምፅ ካለው ናኖ ኢነርጃይዘር ያስተካክለዋል?

ካምቢዮ፣ ትራንስሚሽን፣ ዲፈረንሻል አላስፈላጊ ድምፅ ሊኖረው የሚችለው በሁለት ዋና ምክንየቶች ነው፡፡ ጥረሳጥርሶች፣ ኩሽኔትና ሻፍት ሲበላ እና መጀመርያውኑም የፋብሪካ ስህተት ሲኖር ነው፡፡ በመበላት ምክንያት የተፈጠረን ድምፅ ናኖ ኢነርጃይዘር ስለሚያድሰው ይስተካከላል፡፡ የፋብሪካ ስህተት ምክንያት ከሆነም ብልሽቱ ይሰተካከላል ግን ድምፁ ሙሉ በሙሉ ላይወገድ ይችላል፡፡

24. ናኖ ኢነርጃይዘር የካምቢዮ ማርሽ አቀያየር ላይ የሚሰጠው ጥቅም አለ?

የካምቢዮ ማርሽ ለመቀየር አስቸጋሪ ሲሆን ናኖ ኢነርጃይዘር በመጨመር ሁኔታውን ቀላልና አመቺ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፤ ምክንያቱም ናኖ ኢነርጃይዘር የሴራሚክ ሜታል ወለል ሁሉም አካል (ጥርሳጥርሶች፣ ኩሽኔት፣ ሻፍት፣ ሲንክሮናይዘር፣ ወዘተ) ላይ ስለሚያሰቀምጥ ነው፡፡ ይህ የሴራሚክ ሜታል ወለል መፋቅን፣ መበላትንና፣ ሰበቃን ሰለሚያስቀር ማርሽ ለመለዋወጥ ቀላልና አመቺ ይሆናል፡፡

25. ዘመናዊ በሮቦት የሚንቀሳቀሱ፣ ሜካኒካልና አውቶማቲክ ካምቢዮ ላይ ናኖ ኢነርጃይዘር መጠቀም ይቻላል?

አዎ! በሮቦት የሚንቀሳቀሱ ካምቢዮ፣ ባለ ሁለት ፊሪሲዮን ካምቢዮ ወይም ትራንሰሚሽን ሁሉ ላይ ናኖ ኢነርጃይዘር መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዳውም ለአውቶማቲክ ካምቢዮ “ATF” ለሚጠቀሙ ሁሉ ይሆናል፡፡

26. ናኖ ኢነርጃይዘር በ “self-locking differentials” የ “friction clutches” ሥራን ያውክ ይሆን?

በፍጹም! እንዳውም ናኖ ኢነርጃይዘርን “self-locking differentials” “axles” ላይ መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህ ሲስተም የተሰራው “friction clutches”  “torque transfer” የሚከናወነው በዘይት አማካይነት ሲሆን ናኖ ኢነርጃይዘር ደግሞ የዘይቱን ባህርይ ባለመለወጡ ሥራውን ለማከናወን አያግደውም፡፡

27. ለአውቶማቲክ ካመቢዮ “CVT” ከ “V-belt variable speed drive” ጋር በናኖ ኢነርጃይዘር ሊጠገን ይችላል?

በሚገባ! የ “variable speed drive units” ችግር በፑሊውና በ “V-belt” መካከል ያለው ግንኙነት ሲሆን ናኖ ኢነርጃይዘር እኒህን ብረት ነክ አካላት ከመበላት መከላከል የሚችል ሴራሚክ ሜታል ወለል ስለሚፈጥር መጠገን ይችላል፡፡

28. የኔ ሞተር ሳይክል የተለየ የዘይት ሲስተም አላት፤ ምን ላይ ነው ናኖ ኢነርጃይዘር የምጨምረው?

ኤንጅኑ ባለ 4 ስትሮክ ከሆነ ናኖ ኢነርጃይዘር ዘይት ታንክ ውስጥ ይጨመራል፡፡ ባለ 2 ስትሮክ ኤንጅን ሁለት አይነት ናቸው፤ የተለየ የዘይት ሲሰተም ያለው ወይም ድብልቅ የዘይት ሲስተም ያለው ይባላሉ፡፡ የተለየ የዘይት ሲሰተም ያለው ከሆነ ዘይት ታንክ ውስጥ ይጨመራል፡፡ ድብልቅ የዘይት ሲስተም ያለው ከሆነ በመጠነኛ ዘይት ተለውሶ ነዳጅ ታንክ ውስጥ ይጨመራል፡፡

29. የመኪና አምራች ድርጅቶች ናኖ ኢነርጃይዘር መጠቀምን የደግፋሉ?

የዘመኑ መኪና አለም በቴክኖሎጂ የደረሰችበት ነጸብራቅ ነው፡፡ በየጊዜው የሚጠየቀው የአዳዲስ ሞዴሎች ወደ ገበያ መምጣት የዛሬዎቹ ምርቶች እድሜ አጭር እንዲሆን ይጋብዛል፡፡ በየእለት የሚያጋጥሙን ለውጦች ለምሳሌ እንደ ነዳጅ ጥራት እና የመንገዶች ሁኔታ መኪና ዲዛይን ሲደረግ አይታሰቡም፡፡  ስለሆነም ናኖ ኢነርጃይዘር በመጠቀም እድሜ ማራዘምና አሰተማማኝነትን በማገዙ ይደገፋል፡፡

አብዛኞቹ የመኪና አምራቾች ናኖ ኢነርጃይዘርን ሞክረውት ውጤታማነቱንም አረጋግጠዋል፡፡

ኤንጅን እየተነዳ በራሱ በሚፈጥረው ግፊትና ሙቀት መሠረት ሴራሚክ ሜታል ወለል መፍጠር ቀላልና ርካሽ ነው፡፡ በፋብሪካ ውስጥ እያንዳንዱን የኤንጅን ተሸከርካሪ አካላት በሴራሚክ ሜታል ማጠናከር ግን እጅግ ውድ ሰለሚሆን የመኪና አምራቾች አይሞክሩትም፡፡

30.  ናኖ ኢነርጃይዘር መርዛማ ነው?

አይደለም! ማናቸውንም ምርቶች በምግብ ኢንዱሰትሪ ለመጠቀም የጤና አጠባበቅ የሚፈቅደውን መሥፈርት እስካሟሉ ድረስ ተገቢው ሠርቲፊኬት ይሰጣቸዋል፡፡ ናኖ ኢነርጃይዘር ይህን መሥፈርት ስለማሟላቱ “Material Safety Data Sheet” ይመልከቱ፡፡

MSDS Original Date 2013. 03. 6
Revised Date
Nano Energizer Revise No. 0
Total Pages 1
11 TOXICOLOGICAL

INFORMATION

a. Skin causticity, Irritating(Skin, Eye), mutagenicity: May cause slight irritation in skin and eye, but hazards are little. No other specific information found.

b. Cancer Exposure, Acute Toxicity, Chronic Toxicity, Genital Toxicity, Teratogenicity: Not classified as a carcinogenic substance and no relevant information found.

 

 

 

1,601 total views, 1 views today