የናኖ ቴክ ኢንተርናሽናል ምርቶች

  • -

የናኖ ቴክ ኢንተርናሽናል ምርቶች

Category : Nano

ናኖ ቴክኖሎጂ በተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ተፈጥሮአዊ ንጥረ ነገርን በአቶምና ሞለክዩል ደረጃ የኢንጅነሪንግ ሥራ በማከናወን ለሰው ልጅ ጥቅም ሲባል በመጠን እጅግ ያነሰና (ከ 1 እስከ 100 ናኖ ቢሊዮንኛ ሜትር) የላቀ ውጤት ያለው ምርት መፈብረክ የሚያሰችል የምርምር አድማስ ነው::

ናኖ ኢነርጃይዘር ናኖ ቡሰተር እና ናኖ ማክስ የፋር ኢንፍራሬድ እና ናኖ ቴክኖሎጂን በማጣመር ኤንጅን ለማደስ፣ ነዳጅ ለመቆጠብ፣ ከነዳጅ የሚገኘውን ኀይል መጠን ለማጎልበት እና በነዳጅ አጠቃቀም የሚከሰተውን ድምጽና የከባቢ አየር ብክለት ለማስወገድ የሚያግዙ በናኖ ቴክ ኢንተርናሽናል ኩባንያ የተፈበረኩ የናኖ ቴኬኖሎጂ ኢንጅነሪንግ ምርቶች ናቸው::

የኒህ ምርቶች ባህርይና የሚሰጡት አይነተኛ ጥቅም እንደሚከተለው ቀርብዋል::

ናኖ ኢነርጃይዘር የናኖ በፕላቲነም የተለበጠ ዚርኮኒየም ሴራሚክ እና የናኖ ልቀትና ውህድ ቴክኖሎጂ መሠረት ያደረገ ምርት ሲሆን የመኪና፣ ወዘተ ኤንጅን (ሞተር) ሳይበተን፣ መለዋወጫ ዕቃ ሳያስፈልግ ከኤንጅን (ሞተር) ዘይት ውስጥ በመጨመር ብቻ የተፋቁ፣ የተጫሩና የተበሉ አካላትን በመሙላት ያድሳል ብሎም ጉልበት ይጨምራል፣ የነዳጅና ዘይት ፍጆታን፣ ጩኸትና መርገፍገፍን፣ ከባቢ አየር በካይ ጋዞችን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

ናኖ ቡስተር  የናኖ ወዛምና ጥቃቅን ጠብታ የመፍጠር ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ምርት ሲሆን ከነዳጅ ጋር ሲደባለቅ እራሱን ወደ ናኖ የውሀ ጤዛነት ለወጦ በ 3 ዲ ማትሪክስ በነዳጅ ጋን ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመበተን ከነዳጅ ጋር ተዋህዶ ማቀጣጠያ ቻምበር ሲደርስ በሚያገኘው ሙቀት በመፈንዳት በፒስተኑ ላይ የተጋገረውን ካርቦን በማንደድ ያስወግዳል::

ናኖ ማክስ  የፋር ኢንፍራሬድ እና ናኖ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ መቶ በመቶ ከተፈጥሮ ማዕድን የተፈበረከ በራዲያተር ውሃ ውስጥ የሚጨመር ምርት ሲሆን ነዳጅን ሙሉ በሙሉ በማቃጠል ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ ያስወግዳል፣ በዚያውም የኤንጅን ጉልበት ይጨምራል፣ ነዳጅ ይቆጥባል፣ የመኪናው ማሞቂያና የአየር ጠባይ ማስተካከያ መሣርያዎች ሲከፈቱ ከባክቴርያ የጠራ እና ጥሩ መዓዛ ያለው ንጹህ አየር ይመግባል::